ስልጣንና ተግባር

ስልጣንና ተግባር፡-

ሀ/ ኢንተርፕራይዙ ለፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች (ከጠዋቱ 2፡15 ስራ ቦታ አካባቢ ማድረስ 11፡30 በኋላ ከስራ ቦታ ወደ መኖሪያ  አካባቢ ማድረስ) በአሰሪ  መ/ቤቶች ክፍያ ነፃ አገልግሎት መስጠት፡፡

ለ/ከመንግስት የስራ መግቢያና መዉጫ ሰዓት ዉጭ እንዲሁም በበዓላት ቀናትና ለተለያዩ  የህብረተሰብ ክፍሎች ተመጣጣኝ የትራንስፖርት ታሪፍ በማስቀመጥ ገቢ መሰበሰብ ፣ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት  የገበያ ጥናት በማድረግ ገቢዉን ማሳደግ በገቢዉ መተዳደር፣

ሐ/አገልግሎቱ ለመንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች  ለኩባንያዎች ፣ለትምህርት ቤቶች፣ ለማህበራትና የህዝብ አደረጃጀቶች  ለረዥም ጊዜ የአገልግሎት ጉዞዉን መስመር ርቀት በመለካት  የኮንትራት ዉለታ በመፈራረም  አገልግሎት መስጠት፣

መ/አገልግሎቱ መንግስታዊ ለሆኑና ላልሆኑ ድርጅቶች ፣ለማህበራት፣ ለአደረጃጀቶች፣ ለክበባትና ለግለሰቦች  ለነጠላ ወይም ለደርሶ መልስ ጉዞ አገልግሎት መስጠት፣

ሠ/የጥገና ወርክ ሾፑን  መሳሪያዎችና  ማሽኖች በማደራጀት ለድርጅቱ አነስተኛና ከፍተኛ ተሸከርካሪዎች  አጠቃላይ ጥገናና ዕድሳት አገልግሎት መስጠት፣ የተሸከርካሪ አካል ዕድሳት ፣የቀለም ቅብና ታፒሰሪ ስራዎች መስራት ፣ የተሸከርካሪ ዩኒቶችን  በሞዲፊኬሽንና በማንፋክቸሪንግ  የማምረትና የመጠገን ስራዎች፣

ረ/ከድርጅቱ ዉጭ የሚቀርቡ የተሸከርካሪ ጥገና ጥያቄዎችን በመቀበልና ዉል በመፈራረም  አዋጭ በሆነ ዋጋ  ጠግኖ ለባለ ንብረቱ  ማስረከብን ያካትታል፡፡

ሰ/ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ማረጋገጫ ጥያቄ መቀበል፣ የብቃት ማረጋገጫ ክፍያ ማስከፈል፣ተሸከርካሪዉን በማሽን መመርመር፣ ተሸከርካሪዉንና የምርመራ ዉጤቱን ለሹፌሩ ወይም ለባለንብረቱ ማስረከብ፣

Scroll to Top