የኢንተርፕራይዙ መልዕክት

ተቋማችን በደንብ ቁጥር 17/2009 በከተማው ም/ቤት ፀድቆ በወጣ ደንብ የተቋቋመ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን የሚሰጣቸው አገልግሎቶችም፡-

1ኛ. በባህር ዳር ከተማ ለሚኖሩ በክልሉ የተለያዩ ቢሮዎችና ተቋማት ሠራተኞች

2ኛ. በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ስር ላሉ የተለያዩ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች ተቀጥረው ለሚሰሩ የመንግስት ሠራተኞች

3ኛ. በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ 6ቱ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ተቋማት ለሚሠሩ የመንግስት ሠራተኞች እና:

4ኛ. በሰሜን ጎጃምና በከተማችን ለሚገኙ የፌዴራልና የክልል  ተጠሪ ሲሆኑ ልዩ ልዩ ተቋማት የመንግስት ሠራተኞችን ጥዋት ፣ማታ የሠርቪስ አገልግሎት በመስጠት ዘንዘልማንና ሰባታአሚትን ጨምሮ ሠራተኞች ከሚደርስባቸው የኢኮኖሚ ብዝበዛና መንገላታት እጅጉን የታደገ አዲስና ታዳጊ ተቋም ከመሆኑ በተጨማሪ የከተማችን ሠፊ ህዝብ በተለይም በዝቅተኛ ኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ኗሪዎች በችግር ደራሽ የሆኑ የኤሌክትሪክ  ሞተር የሚሰሩ አውቶብሶችን በማስገባት ህዝቡ በተለይም በነዳጅ መጥፋት ምክንያት በተከሠተ የትራንስፖርት እጥረትና የዋጋ ውድነትን በመቋቋም በቀን ከ20,000 ህዝብ በላይ በማጓጓዝ በሰጠነው አገልግሎት ህዝቡን ከመንግስት ጋር እንዲቆራኝ አድርጎታል፡፡  በአሁኑ ሰዓት ከ137 በላይ ሠራተኞች የሚያስተዳድርና በርካታ ተሸከርካሪዎች ባለቤት የሆነ ተቋም ሲሆን ወደፊትም አዳዲስ ዘመናዊ ተሸከርካሪዎች በማስገባትና አሁን 3ኛ ደረጃ የመኪና ጥገና ጋራዥ አሁን ካለበት የበለጠ በማሳደግና በማዘመን ደንበኞችን ለማርካት በሠፊው አቅዶ ወደ ስራ የገባ ተቋም መሆኑ እንዲታወቅ እንገልፃለን፡፡  

አቶ ዘዉዱ ዘለቀ

ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ

የተመረጡ አገልግሎቶች

አዳዲስ ዜናዎች

የቢሮው አስተዳደሮች

አቶ ዘዉዱ ዘለቀ

ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ

አቶ

ም/ዋና ሥራ አስኪያጅና የትራንስፖርት ኦፕሬሽን የአገልግሎትሽያጭ ዘርፍ አስተባባሪ

አ

ም/ዋና ሥራ አስኪያጅና የቴክኒክአገልግሎትና ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ አስተባባሪ

አ

የኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ኃላፊ

ያግኙን

Scroll to Top