ስልጣንና ተግባር፡-
ሀ/ ኢንተርፕራይዙ ለፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች (ከጠዋቱ 2፡15 ስራ ቦታ አካባቢ ማድረስ 11፡30 በኋላ ከስራ ቦታ ወደ መኖሪያ አካባቢ ማድረስ) በአሰሪ መ/ቤቶች ክፍያ ነፃ አገልግሎት መስጠት፡፡
ለ/ከመንግስት የስራ መግቢያና መዉጫ ሰዓት ዉጭ እንዲሁም በበዓላት ቀናትና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተመጣጣኝ የትራንስፖርት ታሪፍ በማስቀመጥ ገቢ መሰበሰብ ፣ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት የገበያ ጥናት በማድረግ ገቢዉን ማሳደግ በገቢዉ መተዳደር፣
ሐ/አገልግሎቱ ለመንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ለኩባንያዎች ፣ለትምህርት ቤቶች፣ ለማህበራትና የህዝብ አደረጃጀቶች ለረዥም ጊዜ የአገልግሎት ጉዞዉን መስመር ርቀት በመለካት የኮንትራት ዉለታ በመፈራረም አገልግሎት መስጠት፣
መ/አገልግሎቱ መንግስታዊ ለሆኑና ላልሆኑ ድርጅቶች ፣ለማህበራት፣ ለአደረጃጀቶች፣ ለክበባትና ለግለሰቦች ለነጠላ ወይም ለደርሶ መልስ ጉዞ አገልግሎት መስጠት፣
ሠ/የጥገና ወርክ ሾፑን መሳሪያዎችና ማሽኖች በማደራጀት ለድርጅቱ አነስተኛና ከፍተኛ ተሸከርካሪዎች አጠቃላይ ጥገናና ዕድሳት አገልግሎት መስጠት፣ የተሸከርካሪ አካል ዕድሳት ፣የቀለም ቅብና ታፒሰሪ ስራዎች መስራት ፣ የተሸከርካሪ ዩኒቶችን በሞዲፊኬሽንና በማንፋክቸሪንግ የማምረትና የመጠገን ስራዎች፣
ረ/ከድርጅቱ ዉጭ የሚቀርቡ የተሸከርካሪ ጥገና ጥያቄዎችን በመቀበልና ዉል በመፈራረም አዋጭ በሆነ ዋጋ ጠግኖ ለባለ ንብረቱ ማስረከብን ያካትታል፡፡
ሰ/ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ማረጋገጫ ጥያቄ መቀበል፣ የብቃት ማረጋገጫ ክፍያ ማስከፈል፣ተሸከርካሪዉን በማሽን መመርመር፣ ተሸከርካሪዉንና የምርመራ ዉጤቱን ለሹፌሩ ወይም ለባለንብረቱ ማስረከብ፣
